የግል ዘርፍ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ የግል ዘርፍ ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ

የግሉ ዘርፍ እንደሃገር የሚጠቀምበትን አስተዋፅኦ በሚገባ እንዲወጣ ለማድረግ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ መደገፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፤በርካታ በኢኮኖሚ በፍጥነት ያደጉ ሃገሮች የተቀናጀ ጥናትን መሰረት ያደረገ ድጋፍ ለግሉ ዘርፍ በማድረግ ከፍተኛ ውጤት አግኝቷል፡፡ በመሆኑም ይህ የስራ ሂደት ይህን ሃላፊነት ይወጣ ዘንድ ይጠበቃል፡፡

 

ዋና ዋና ተግባራት

 

ምርታማነትን ለማሻሻል የሚጠቅሙ ቴክኖሎጂዎችን የሚያለሙና የሚያስገቡ የግሉ ዘርፍ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል

 

ለግሉ ዘርፍ በፍጥነት ማደግ እንቅፋት የሆኑ አሰራሮችንና ሌሎች ማነቆዎችን በመለየትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንዲፈቱ በማድረግ የግሉን ዘርፍ በፍጠነት እንዲያድጉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር።

 

በቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢንቬስት ለሚያደርጉ የግል ዘርፎች ማበረታቻ ስርዓቶችን መዘርጋት

 

የሀሪቱን የአገልግሎት የኢኮኖሚ ሴክተር ሊደገፉ የሚችል አስቻይ ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመጠቀም የግሉ ዘርፍ ዋና ተዋናይ እንዲሆን መደገፍ

 

የሀገር ውስጥ የሚለሙ ቴክኖሎጂዎች ጥራታቸውንና ተወዳዳሪነታቸውን በማረጋገጥ ከውጪ የሚገቡትን በመተካት የውጪ ምንዛሪ ወጪ ማስቀረት የሚቻልበትን ሁኔታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ማመቻቸት