News News

​አወስትራሊያ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታን የመፍጠር እንቅስቃሴን እደግፋለሁ አለች፡፡

አወስትራሊያ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታን የመፍጠር እንቅስቃሴን እደግፋለሁ አለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር አወስትራሊያ ድጋፍ በምታደርግባቸው መስኮች ዙሪያ በኢትዮጵያ የአወስትራሊያ አምባሳደር ከሆኑን ፒተር ዶይል ጋር መክረዋል፡፡
ውይይታቸው ቴክኖሎጂ በሚጠቀም ግብርና፤ የእንስሳት ሃብት እና የዲጂታል የመሬት ምልከታ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡
አወስትራሊያ የ30 አመት መረጃዎችን ሊያሳይ የሚችል ዲጂታል የመሬት ምልከታ
ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሀገር በመሆኗ ይህንን ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ዝግጁ መሆኗን አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡
ቴክኖሎጂው የከርሰ ምድር ውሃና ማዕድን ያለበትን ቦታ መለየት የሚያስችል፣
የአፈር ሁኔታን ለመለየትና የደን ሃብትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር ቴክኖሎጂ በሚጠቀም የመስኖ ልማትና በእንስሳት ሃብት ልማት መስክ የአውስትራሊያ ባላሃብቶች በኢትዮጵያ እንዲሰማሩና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር ጠይቀዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው  ዲጂታል የመሬት ምልከታ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ መዘርጋት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ቴክሎጂውን በአፍሪካ ለመዘርጋት የሚንቀሳቀሰውን ቡድን ከሚመሩት አዳም ሊውስ (ዶ/ር) ጋር መምከራቸው ይታዋሳል፡፡

Archive news Archive news