News News

​ካናዳ የሴቶችን ጫና በሚያቃልሉ ቴክኖሎጂ ዝርጋታ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ስራ እደግፋለሁ አለች፡፡

​ካናዳ የሴቶችን ጫና በሚያቃልሉ ቴክኖሎጂ ዝርጋታ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ስራ እደግፋለሁ አለች፡፡
በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር አንቶኒ ቼቭሬ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መክረዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተለያዩ ክልሎች ባደረገው ጥናት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ የቴክኖሎጂ ልየታ አድርጓል፡፡
አምባሳደሩ እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ለመዘርጋት የሚደረገውን ጥረት ካናዳ ትደግፋለች ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በድረ-ገፅ ማበልፀግና በስራ ፈጠራ እየሰለጠኑ ያሉ ሴቶችንም ፕሮጀክቶቻቸው ታይቶ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በማገናኘት ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍ እንደሚያርጉ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ‹‹ቴክኖሎጂ ለሴቶች፣ ሴቶች ለቴክኖሎጂ›› በሚል በየክልሉ የሚኖሩ ሴቶችን ጫና በመለየት ችግራቸውን የሚያቃልል የቴክኖሎጂ ዝርጋታ ለማከናወን እቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

Archive news Archive news