News News

Back

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የዌብ ፖርታል ስልጠና ሰጠ ::

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የዌብ ፖርታል ስልጠና በካፒታል ሆቴል ሰጠ ፡፡ ስልጠናው በሁለት ዙር የተካሄደ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ከግንቦት 22 እስከ ግንቦት 24 /2010 ዓ.ም ድረስ ፣ ሁለተኛው ዙር ደግሞ ከግንቦት 27 እስከ ግንቦት 29/2010 ዓ.ም ድረስተሰጥቷል፡፡በመጀመሪያው ዙር 70 ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ደግሞ ተጨማሪ 70 ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡

የስልጠናው መጀመርን አስመልክቶ ክቡር አቶ ሲሳይ ቶላ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚ/ር የተሠጠውን ስልጣንና ኃላፊነት መሠረት በማድረግ በርካታ የወል መጠቀሚያ መሠረተ ልማቶችን ሲያለማ ቆይቷል በማልማትም ላይ ይገኛል፡፡ ከተለሙ መሰረተ ልማቶች ውስጥ የብሔራዊ ዳታ ማዕከል ልማትና አስተዳደር፣ የወረዳ ኔት ልማትና አስተዳደር፣ የልዩ ልዩ ፌደራል ተቋማት የአካባቢ ኔትወርክ ልማት፣ የትራንዛክሽናል ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶች ፕላትፎርም ልማትና የመንግስት ፖርታሎች ልማት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው እንደተናገሩት ሚኒስቴር መ/ቤቱ በ2010 በጀት ዓመት በትኩረት በመስራት ላይ ከሚገኛቸዉ ተግባራት መካከል የመንግስት ፖርታሎችን ማሻሻልና ጥራታቸውን ጠብቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል አንዱ ሲሆን ለዚህ ይረዳ ዘንድ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ለተለያዩ የሚኒስቴርና የፌደራል ተቋማት በመስጠት የክህሎት ክፍተትን ለመሙላትና የፖርታሎቹን ጥራት ለመጠበቅ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ፖርታሎችን ማልማት መሰረታዊ ጉዳይ ሆኖ በየተቋማቱ ያሉ የመረጃ ምንጭ የሆኑት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስለዌብ ፖርታል አጠቃቀም በቂ ግንዛቤና ክህሎት ሊኖራቸው ግድ እንደሚልና የሚሰጠው ስልጠናም መረጃ አቅራቢ ባለሙያዎች በፖርታሎች ላይ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ በአግባቡ መገልገል እንዲችሉ የሚስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.

News Archive News Archive