News News

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተቀናጀ የእንስሳት ሀብት ልማት በሶማሌ ክልል ሊጀመር ነው።

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተቀናጀ የእንስሳት ሀብት ልማት በሶማሌ ክልል ሊጀመር ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር÷ የሶማሌ ክልል መንግስት እና የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ አብሮ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ መሰረት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማቅረብ÷ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እንስሳቱን የማዳቀል ስራዎችን የሚሰሩ ሲሆን የክልሉ መንግስት ደግሞ ማህበረሰቡን የማስተባበርና የገንዘብ ደጋፍ የማድረግ ስራ ይሰራል።
የእንስሳት ሀብት ልማቱ በመጀመሪያ በተመረጡ በክልሉ ሶስት ወረዳዎች ተግባራዊ ይደረጋል።
በክልሉ ያሉ አርብቶ አደሮች ከእንስሳት ሃብታቸው ተጠቃሚ አይደሉም ያሉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሞሀመድ ፕሮጀክቱ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ያግዛል ብለዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) ሰፊ የእንስሳት ሃብት ያለውን ክልል ከሀብቱ ህዝቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት ገበያ ማዳረስንም ታሰቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ)÷ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሞሀመድ እና የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ ኤልያስ ኡመር ፈርመውበታል። 
ይህ ፕሮጀክት በትግራይ ክልል ተግባራዊ ሆኖ ውጤት የተመዘገበበት ሲሆን በቀጣይ በሌሎች ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል።

Archive news Archive news