News News

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ‹‹የኢኖቬሽን ደን›› አሻራቸውን አሊልቱ አካባቢ በሚገኝ ተራራ ላይ አኑረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ‹‹የኢኖቬሽን ደን›› አሻራቸውን አሊልቱ አካባቢ በሚገኝ ተራራ ላይ አኑረዋል፡፡
ሰራተኞቹ በኦሮምያ ክልል አሊልቱ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ተራራ ላይ 17ሺ 887 ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡


በሀገር አቀፍ ደረጃ 4ቢሊን ችግኝ ለመትከል በተያዘው እቅድና በቀን 200ሚሊን ችግኝ በላይ በመትከል የአለም ክብረ ወሰን በተሰበረበት ታሪክ ላይ በመሳተፋው ደስተኞች መሆናቸውን ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ወቅት የችግኝ አጥረት ማጋጠሙንም ጠቁመዋ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር ከችግኝ መትከል ባለፈ ፀድቀው ጥቅም እንዲሰጡ ማድረግ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የችግኞቹን መፅደቅ የሚከታተከልና እንክብካቤ የሚያደርግ ቡድን ይቋቋማል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በየአመቱ በቦታው ላይ ችግኞችን በመትከል የኢኖቬሽን ደናችንን እናለማለን ብለዋል፡፡


Archive news Archive news