News News

​ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የስራ እድል ፈጠራን ለማገዝ የሚያስችል የ100 ሚሊየን ዶላር ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የስራ እድል ፈጠራን ለማገዝ የሚያስችል የ100 ሚሊየን ዶላር ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የከሊፋ ፈንድ የቦርድ ሰብሳቢ ሁሴን ጃዚም አል ኖዌስ ተፈራርመውታል።
ትብብሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ግብርና፣ ጤና፣ ማምረቻ ዘርፍ፣ ኢነርጂ እና በአይሲቲ ዘርፍ ላይ የስራ እድል ፈጠራን ለማገዝና ለማበረታታት የሚውል ነው፡፡
በአይሲቲ ዘርፍ በተለይ በባሉበት ግብይት (e-commerce) የሚደረግ የንግድ ልውውጥን ማዘመን የትብብሩ አካል ነው፡፡
የከሊፋ ፈንድ የቦርድ ሰብሳቢ ሁሴን ጃዚም አል ኖዌስ ከኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር ኢንጂ.) ጋር ወደ ስራ መግባት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል፡፡

Archive news Archive news