News News

Back

ሰኔ 24፣ 2010 ዓ.ም የለሙ የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችን ለመተግበር ዝግጁ ከሆኑ አምስት የፌዴራል ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ ::

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለሁለተኛዉ ጊዜ በተካሄደዉ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ኤክስፖ ኢትዮጵያ ላይ ሰኔ 24 ቀን 2010 ዓ.ም ከመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ባካሄደዉ የዉይይት መድረክ ላይ ለደንበኞች በኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታቸዉን ካጠናቀቁ አምስት የፌደራል ተቋማት ጋር የመግባባቢያ ሰነድ በሚሊኒየም ላሊበላ አዳራሽ ተፈራረመ፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመዉ ከዉኃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፣ከግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር ፣ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር ሲሆን ይህ የአሰራር ዘዴ ለደንበኞች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ፈጣን፣ቀልጣፋና ምቹ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ የስምምነት ፊርማዉ የተካሄደዉ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታዉ በክቡር አቶ ሲሳይ ቶላና በየተቋማቱ ሀላፊዎች አማካኝነት ነዉ፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ይህ ቅንጅታዊ አሰራር የቴክኖሎጂ ዕድገትን ታሳቢ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ለማዘመን ከፌደራል መስሪያ ቤቶች ባለፈ ከሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋርም እንደሚቀጥል ውይይቱን በመሩት በክቡር አቶ ሲሳይ ቶላ፣የልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እና ክቡር ዶ/ር መብራቱ ገብረማርያም፣የሬጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተጠቁሟል፡፡

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.

News Archive News Archive