የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችና አፕሊኬሽኖች ልማትና አስተዳደር የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችና አፕሊኬሽኖች ልማትና አስተዳደር

የተለያዩ የመንግስት ተቋማት አሰራራቸውን እና አገልግሎታቸውን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ የኤሎክትሮኒክስ አገልግሎቶችን እና አፕልኬሽኖችን የማልማት ፣ የማስተባበር እና የማስተዳደር ስራዎች ያከናውናል፡፡ 
 
ተግባርና ሃላፊነት

  •  መንግስት ለዜጎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ምቹ፣ ቀልጣፋና ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የኤሌክትርኒክስ አገልግሎቶችና ሲስተሞች ያስትባብራል፣ያለማል፣ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፣
  •  መንግስት ለዜጎች መረጃ ተደራሽ ለማድረግና በመንግስት አሰራር ያለቸው ተሳተፎ ለማሳደግ  የሚያስችሉ እንፎርሜሽናል ፖርታሎች እና አማራጭ የመረጃ ማሰራጫ  ቻናሎች ያስተባብራል፣ ያለማል፣ ለብዙሃኑ ህብርተስብ  አገልግሎት እንዲሰጡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፣
  •  የሶፍትዌር አፕሊኬሽኖችና ኤሌክትሮኒክ ሰርቪሶችን ለማልማት፣ ለመጠቀምና ለማስተዳደር የሚያስችሉ የዲዛይን፣ የዴቬሎፕመንት፣ ቴስቲንግና ፕሮጄክት ማኔጅመንት አቅሞችን ይገነባል፣ አስፈላጊ የሆኑ የአሰራር ስርአቶችን፣ ላቦራቶሪዎችና መሰረተ-ልማቶችን ያዘጋጃል፣ ምቹ ኢንቫይሮመንት ይፈጥራል።
  •  አዳዲስ የሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች እና ኤሌክትሮኒክስ መንግስት መፍትሄዎችን በጥናት ይለያል። ከሀገራዊ ፍላጎት የማጣጣምና ጥቅም ላይ የማዋል ስልቶች ይነድፋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል።   
  •  በሀገሪቱ ተግባራዊ የሚደረጉ የኤሌክትሮኒክስ መንግስት አገልግሎቶች ጥራት፣ ወጥነትና ተናባቢነት እንዲኖራቸው የሚያስችል ስታንዳርድ ያወጣል፣ የማስፈጸምያ ስረአት ይዘረጋል፣ ይከታተላል
  •  አገልግሎታቸው አገር አቀፍ የሆነ፣ ተቋም ተሻጋሪና የጋራ መጠቀሚያ የሆኑ ትላልቅ የመንግስት የሶፍትዌር ፕሮጄክቶች፣ ሲስተሞችና አፕሊኬሽኖች ትግበራን በሃላፊነት የመምራትና ማስተባበር ተግባራትን የፈጽማል፣ እንደ አስፈላጊነቱ ያስተዳድራል።