የመንግስት የኢኮቴ ኔትዎርክ ልማትና አስተዳደር የመንግስት የኢኮቴ ኔትዎርክ ልማትና አስተዳደር

የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸውን ተደራሽ ለማድረግ እና ግንኙነታቸውን ለማቀላጠፍ የሚያስፈልጉ የኢኮቴ መሰረተ ልማት ስራዎችን ያለማል ያስተባብራል እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ያስተዳድራል፡

 

ተግባርና ሃላፊነት

 

  • በሀገር ደረጃ የሚከናወኑ የመንግስት የኢኮቴ ኔትዎርክ ለማስፋፋት ለማቀናጀት ደረጃቸውንየጠበቁና ተናባቢ ለማድረግ የሚያስችሉ የግንኙነት ኢንፍራስትራክቸር ልማት ፍኖተ-ካርታ ፣የኢንተርፕራይዝ አርክቴክቸር የኢንተርኦፕሬቢሊቲ ስታንዳርዶችና ሌሎች የዘርፉን ዘመናዊነት ለማስጠበቅ የሚያገለግሉ ማዕቀፎችና ስረአቶች እንዲዘጋጁ ሲጸድቁም ተግባራዊ እንዲሆኑ ስራውን በሃላፊነት ይመራል፣ ሌሎችንም ያስተባብራል፡፡
  • የመንግስትን የግንኙነትና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሳለጥ የመንግስትን ተግባር ለመደገፍና ተቋማት እርስ በእርስ ለማሰተሳሰር የሚያገለግሉ የመንግስት የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማቶች (Government Nets) እንዲዘረጉ ይመራል፣ ያስተባብራል፣
  • የመንገግስት ተቋማት የግንኙነት መሰረተ-ልማቶች የመረጃ ስረአቶችና ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የደህንነት ማስጠበቅያ ፖሊሲዎች ስታንዳርዶች እና ፕሮሲጀሮች እንዲዘጋጁ ሲጸድቁም ተግባራዊ እንዲሆኑ ስራውን በሃላፊነት ይመራል (ያዘጋጃል)
  • ለመንግስት ተቋማት የወል አገልግሎት የሚውሉ የኢኮቴ መሰረተ-ልማቶች ዝርጋታ ጥገና፣ የዴታና ባንድ ዊድዝ ፍጆታ የሚያስፈልግ በጀት በማዕከል እንዲያዝና እንዲተዳደር ከሚመለከተው አካልበትብብር ይሰራል፣
  • በሁልም የመንግስት ተቋማት ጠንካራ የኢኮቴ ድጋፍ ቡድን እንዲዋቀር አስፈላጊው የቴክኒክና የማማከር ድጋፍ ያደርጋል፣ 
  • በመንግሥታዊ ተቋማት የመረጃ ሥርዓትን ከመገንባትና ከማቀናጀት አንፃር የመንግሥት የዶሜይን ስም (Government domain name) ይደለድላል፣ አድራሻ ይሠጣል፣ ይመዘግባል፣ ይቆጣጠራል፡:
  • ዘመናዊና ወቅታዊ የሆኑ አዳዲስ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት የተመለከቱ ግኝቶች ያጠናል፣ ከሀገሪቱ ፍላጎት የማጣጣም ወደ ሀገር የማስገባት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረጊያ ስልቶች ይነድፋል ይተገብራል፡፡
  • በመንግስት ተቋማትና በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢዎች መካከል በሚነሱ የአገልግሎት ፍላጎቶች እንደ ድልድይ በማገልገል መሠረታዊ የግንኙነት አገልግሎቶች በተገቢው መንገድ ሳይቋረጥ እንዲቀርብ ከተቋማቱ ጋር በጋራ ይሰራል፡፡
  • አገልግሎታቸው አገር አቀፍ የሆነ፣ ተቋም ተሻጋሪና የጋራ መጠቀሚያ የሆኑ ትላልቅ የመንግስት የግንኙነት መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ፕሮጄክቶች ትግበራ በሃላፊነት የመምራትና ማስተባበር ተግባራትን ይፈጽማል፣ እንደ አስፈላጊነቱ ያስተዳድራል።