ብሔራዊ የመረጃ ቋት ልማትና አስተዳደር ብሔራዊ የመረጃ ቋት ልማትና አስተዳደር

የብሔራዊ ዳታ ማዕከል አስተዳደር የተሠጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ለስራው የሚያግዙትን በማዕከሉ ያሉትን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሀብቶችን ያስተዳድራል እንዲሁም ደህንነታቸውን ይጠብቃል፡፡ 
 

ተግባርና ሃላፊነት

  • የብሔራዊ ዳታ ማዕከል ለማልማትና ለማስተዳደር የሚያስፈልጉ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ስታንዳርዶችና አሰራሮችን እንዲዘጋጁ፣ ሲጸድቁም ተግባራዊ እንዲሆኑ ስራውን በሃላፊነት ይመራል፣ ሌሎችንም ያስተባብራል፣ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፡፡
  • በብሔራዊ ዳታ ማዕከል የሚገኙን የኔትዎርክ መሠረተ ልማቶች፣ ኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን አፕሊኬሽኖች የሚያስፈልጉ ሪሶርስ በተቀመጡት ስታንዳርዶች መሠረት 24/7 አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማስቻል፣ ችግሮች ሲያጋጥም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባባር መፍትሔ ይሰጣል፡፡
  • በማዕከሉ የሚገኙትን ሲስተም አድሚንስትሬተሮችን ያስተዳድራል፤ የሚያስተዳድራቸውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሀብቶችን ላይ የቅድመ መከላከል እና የማስተካከያ ጥገናዎችን ያከናውናል፤ እንዲሁም በማዕከላቱ የሚገኙትን አጠቃላይ ሀብቶችን ያስተዳድራል፡፡
  • በሌሎች የሀገሪቱ  ለሚገኙ ዳታ ማዕከሎች  እንደአስፈላጊነቱ ድጋፍና የማማከር ስራ ያከናውናል፡፡