ምርትና አገልግሎት ኢንጂነሪንግ ምርትና አገልግሎት ኢንጂነሪንግ

በዚህ መስክ አገልግሎትና ምርት መሆን የሚችችሉ ቴክሎጂዎች ከሃሳብ ጀምሮ እንዲደገፉና እንዲለሙ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡ 

የሃርድዌር እና ሶፍትዌር ዲዛይን፤ የምርትና አገልግሎት ፕሮቶታይፐሮች እንዲወጡ ማድረግ፤ የምርትና አገልግሎት ምህንድስና በተጨባጭ እንዲኖር የሚያስችል ዘርፍ ነው፡፡ በተጨማሪም በማማከርና ቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ረገድም ይህ ክፍል በዲዛይን፤ በፕሮቶታይፕ ዴቬሎፕመንት፤ በገባያ ማፈላለግ፤ ወደምርት ለመቀየር፤ ቢዝናስ ፕላን አዘገጃጀት ወዘተ የምክር አገልግሎትና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ወደ አገልግሎትና ምርት የሚቀየሩ ዲዛይኖች፤ የለሙ ሲስተሞችና አገልግሎቶች ጥራታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ፤ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፤ ወደ ምርትና አገልግሎቶች የሚሸጋገሩ የቴክኖሎጂ ውጥኖችና ውጤቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑና በሌሎች አካላትም ጭምር በተመሳሳይ መልኩ የሚሰሩትን ቁጥጥር ማድረግ፡

 

ተግባርና ሃላፊነት የምርትና አገልግሎት ኢንጂነሪንግ የስራ ክፍል ሚከተሉት ተግባራትና ሃላፊነቶች ይኖሩታል፡

  • ወደ አገልግሎትና ምርት የሚቀየሩ ዲዛይኖች፤ የለሙ ሲስተሞችና አገልግሎቶች ጥራታቸው የተጠበቀ ማረጋገጥ፤ የትክኖክ ድጋፍ መስጠት፤ አገልግሎትና ምርት መሆን የሚችሉ ቴክሎጂዎች ከሃሳብ ጀምሮ እንዲደገፉና እንዲለሙ ማድረግ፡፡
  • ሃርድዌር እና ሶፍትዌር ዲዛይን፤ የምርትና አገልግሎት ፕሮቶታይፐሮች እንዲወጡ ማድረግ፤ ጥራት ያላቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ
  • የምርትና አገልግሎት ምህንድስና በተጨባጭ እንዲኖሩ ማስቻል
  • የምርትና አገልግሎት ኢንጂነሪንግ ዘርፍ በማማከርና ቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
  • በማናችውም የምርትና አገልግሎት ዘርፎች የሀገራዊ አቅም ማጎልበትና የአቅም ግንባታ ማካሄድ የሚችል አቅም መፍጠር