የኢኮቴ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ የኢኮቴ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ

ይህ ዘርፍ የኢኮቴ ሴክተር ፖሊሲና እስትራቴጂ መሰረት በማድረግ በመንግስት ተቋማት የመገናኛ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ መንግስት ለዜጎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በኢኮቴና ኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ተደግፈው ምቹ፣ ቀልጣፋና ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን ይቀርጻል፣ ያስፈጽማል፣ ብሔራዊ ይመረጃ ቋት ያለማል፣ ያስተዳድራል፣ በሌሎችም የመንግስት ተቋማት ሊኖሩ የሚገባቸውን የመረጃ ቋቶችን ደረጃ ይውስናል፣ ከበሔራዊ የመረጃ ቋት ጋር ሊኖራቸው ስልሚችለው ገንኙነት ስርዓት ይዘረጋል። ለመንግስት ተቋማት የሚደረጉ የኢኮቴ መሰረተ-ልማቶች፣ የሶፍትዌር አፕሊኬሽኖችና ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶች ተናባቢነታቸው፣ ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና አስተማማኝነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን እስታንዳርድ እንዲዘጋጅላቸው ያደርጋል፣ አፈጻጸማቸው ይከታተላል።

የአገሪቱን የከፍተኛውን ደረጃ መለያ ዶሜይን ስም ሀገራዊ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲፈጠርና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚመለከቸውን ያስተባብራል፣ ለአፈፃፀሙም እገዛ ያደርጋል፤ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና አገልግሎቶች በማጥናትና በመለየት እንዲስፋፉና ጥቅም ላይ እንድውሉ ያደርጋል፤በመንግስታዊ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትን ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲቻል የሥልጠና እና የፕሮጀክት አስተዳደርና አፈጻጸም ምክር ይሰጣል።