የምርታማነት ቴክኖሎጂ ፍላጎት ዳሰሳ፣ ትንተናና ድጋፍ የምርታማነት ቴክኖሎጂ ፍላጎት ዳሰሳ፣ ትንተናና ድጋፍ

በቴክኖሎጂ ዘርፍ የማደፋክቸረሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ጥናትን መሰረት ያደረገ ፍለጎት ዳሰሳ ማድረግና ዳሰሳውን መሰረት ያደረገ ለመፍትሔ እርምጃ በሚያመች መንገድ መተንተን ያስፈልጋል።  በመንግስትና በግል አምራች ተቋማት የተለዩ ፍላጎቶችን ምላሽ በመስጠት አቅማቸውን ዘላቂ በሆነ መንገድ መገንባት፣ ማዘመንና ተወዳዳሪ ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል፤ በተሳለጠ መንገድ ቴክኖሎጂን የሚጠቀመው አምራች ዘርፍ ለኢኮኖሚ የሚፈለግበትን ኣስተዋፅኦ በቂ የስራ እድል በመፍጠር ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት እንዲሁም የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት ይሰራል፡፡ በዚህ ረገድ የዳሰሳ ጥናትና ትንተና ሰነዱን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ድጋፍ ስልጠናና ትስስር በመፍጠር የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ይጠበቃል፡፡ 
 
ተግባር እና ሃላፊነት

  •  ትኩረት የሚፈልጉና ለምርታማነት ማሻሻያ የሚሆኑትን የማኑፋክቸሪንግና የአገልግሎት ቴክኖሎጂዎችን ይለያል፣ ይተነትናል፣ ይደግፋል፣ 
  •  በማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ምርታማነትን ማሻሻል ለማስቻል በቴክኒክና ክህሎት አቅም ማሳድግ የሚቻልበትን ስርዓት ይዘረጋል፣ ይደግፋል፣ ያበረታታል
  •  ተግባርና ሀላፊነቱን ለመወጣት ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ትስስሮችን ይመሰርታል፣ በማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት የቴክኖሎጂ ሽግግር ያሳድጋል 
  •  በሀገሪቱ የሚገኙትን የምርታማነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎች መረጃዎች ይመዘግባል፣ ይከታተላል፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ያላቸውን አስተዋትዖ ይከታተላል፣ የገምግማል፣ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ዳሰሳ ጥናቶችን ያደርጋል፣