ኢንኩቤሽን ልማትና አስተዳደር ኢንኩቤሽን ልማትና አስተዳደር

 

ለቴከኖሎጂ ስራ ፈጠራ፤ ለንግድ ወይም ለጅምር ሰታርትአፕ እድገት አገልግሎቶችን የሚሰጥና ለዘርፉ የሚመጥን የስራ አከባቢን የሚያመቻች ዘርፍ ነው፡፡ አዲስ የቴክሎጂ ጅምሮች ስኬታማ እንዲሆኑ ያግዛል በዚህም የኢንኩቤሽን ማእከላትን መክፈት፤ የአሰራር ስርአት መዘርጋት፤ ማጠናከር፤ የተመረጡ ተጠቃሚዎችን ማስገባት፤ ሲጨርሱ እንዲወጡ ማድረግና ስራ ፈጠራና ገበያ ተኮር እንዲሆኑ ይሰራል፡፡
 
ይህ ዘርፍ ለፈጠራ ባለሙያዎች እስከ ፕሮቶታይፕ ማዉጣት የሚያደርስ የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፤ መሰረተ-ልማት (የስራ ቦታ፤ ኮምፒውተሮች፤ ኢንተርኔት ወዘተ)፤ በማቅረብና አመራር በመስጠት ያግዛል የንግድ ስራ ስትራቴጂ እና የገበያ ትስስር መፍጠር፡ የገበያ ጥናትና ምክር፤ ከአዳዲስ ካፒታል /መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ጋር ማዛመድ፤ማያያዝ፤ የአዕምሮ ንብረት (አይ.ፒ) ምክር አገልግሎት፤ የህግ ምክር አገልግሎት የመስጠት ተግባርም ያከናውናል፡፡ ይህ ክፍል በኢንኩቤሽን ማእከላት የሚገቡትንና ዘርፉ በተቃሚነታቸው የለያቸውን የቅድመ-ምርት (ፕሮቶታይፕ) ውጤቶች በኢንዱስተሪዎች እንዲታወቁ፤ አብረው እንዲሰሩ፤ የገበያ አማራጭ እንዲፈጠርላቸው ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ የ መንግስትና የግል ዘርፍ ትስስር እንዲኖር ያደርጋል፡፡
 
ተግባራትና ሃላፊነቶች
 
የኢነኩቤሽን ልማትና አስተዳር የስራ ክፍል ሚከተሉት ተግባራትና ሃላፊነቶች ይኖሩታል፡
ኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማለትም ለቴከኖሎጂ ስራ ፈጠራ፤ ለንግድ ወይም ለጅምር ሰታርትአፕ እድገት አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማትና ማዕከላትን ማልማትን ማስተዳደር፡
ለፈጠራ ባለሙያዎች እስከ ፕሮቶታይፕ ማዉጣት የሚያደርስ የማምረቻ ከባቢ ሁኔታን መፍጠርና አመራር መስጠት፤
የንግድ ስራ ስትራቴጂ እና የገበያ ትስስር መፍጠርና የገበያ ጥናት ምክር፤ ከአዳዲስ ካፒታል /መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ጋር ማዛመድ፤ማያያዝ፤ የአዕምሮ ንብረት (አይ.ፒ) ምክር አገልግሎት፤ የህግ ምክር አገልግሎት
ኢንኩቤሽን ማዕከላት በግል፣ በዩኒቨርስቲዎች፤ እና በክልሎች፤ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠናዎች እንዲመሰረቱና ከበሔራዊ የኢኖቬሽን ስርዓት ግንባታ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል