አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች ቁጥጥርና አስተዳደር አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች ቁጥጥርና አስተዳደር

ሃገሪቱ የምትከተለውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ከግብ ለማድረስ ይህ የስራ ሂደት በቴክኖሎጂ ዘርፍ የበኩሉን ሚና በውጤታማነት እንዲወጣ ይጠበቃል፡፡ ግቡን ለማሳካት በሚያስችለው ቁመና ይደራጃል፡፡ በዋናነት ወደ ሃገሪቱ የሚገቡና ጥቅም ላይ የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችና የቴክኖሎጂ ውጤቶች አጠቃቀም፣ ለምርት ሂደት አወጋገድ ወቅታዊ ባልሆነ መንገድ እንዲተገበር ድጋፍና የቁጥጥር ስራ ይሰራል፡፡ ስርዓት መዘርጋት ሂደት ያግዛል፡፡ 
 
ተግባርና ኃላፊነት

  •  ከሀገሪቱ ለአየር ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ለመተግበር በሚያስችል መልኩ ልዩ ትኩረት አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችን፣ ይለያል፣ ይከታተላል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ይደግፋል፣ 
  •  ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በመተባበር በካይ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችና የቴክኖሎጂ ምርቶችን ማቀብና ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ሊያደርግ የሚቻልበትን ስርዓት ይዘረጋል፣ ያስተባብራል፣ ይደግፋል
  •  ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር በመተባበር ሀገር ውስጥ የገቡና በስራ ላይ ያሉ በካይ ቴክኖሎጂዎችና የቴክኖሎጂ ምርቶች የሚወገዱበትን፣ በማዕከል የሚሰባሰቡበትንና፣ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉበትንና፣ የሚወገዱበትን ስርዓት ይዘረጋል፣